እስከ 18 ዓመት ዕድሜ ድረስ ነፃ የጥርስ ህክምና- ይገባዎታል!
“ክላሊት ስማይል” አቅርቦላችኋል፤ ለወላጆች ሙሉ መምሪያ – በጤና ጥቅል ውስጥ የተካተቱ በነፃ ወይም በአነስተኛ የግል ተሳትፎ የሚቀርቡ የጥርስ ህክምናዎችን ያካተቱ፤ ሁሉም የብሔራዊ የጤና ኢንሹራንስ ሕግ ድንጋጌዎችን የተከተሉ ናቸው።
በ 2010፣ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ በጤና ጥቅል ውስጥ ነፃ የልጆች የጥርስ ህክምና ተካተተ፣ እና ከዚያ ጊዜ ጀምሮ፣ የተሻለ የአፍ ንፅህናን በማስጠበቅ ረገድ የተሻለ የግንዛቤ መጨመርን መታዘብ ችለናል፣ እና በእስራዔል የልጆች የጥርስ ሁኔታ ከባለፉት ጊዜያት አንጻር የተሻለ ሆኗል።
የሚከተለው አንቀፅ እስከ 18 ዓመት ዕድሜ ድረስ ያሉ ልጆች ሊያገኟቸው ስለሚችሏቸው ስለ መከላከል እና ስለ ማቆያ የጥርስ ህክምናዎች የሚያስረዳ ነው፣ ይኸውም በነፃ ወይም በአነስተኛ ክፍያ የሚደረግ ሲሆን፣ የብሔራዊ የጤና ኢንሹራንስ ሕግ መሰረት ነው።
ብሔራዊ የጤና ኢንሹራንስ ሕግ ምንድነው
ብሔራዊ የጤና ኢንሹራንስ ሕግ ከልጆች ነፃ የጥርስ ህክምና ጋር የተያያዘ ሲሆን፣ በ ጁን 2010 በክንሰት የፀደቀ ጠቃሚ ሕግ ነው እና አሁን ላይ እስከ 18 ዓመት ዕድሜ ላሉ ልጆች፣ ነፃ ወይም በአነስተኛ የግል ተሳትፎ የጥርስ ህክምና የሚያገኙበት ነው፣ ይኸውም በጤና ጥቅል መሰረት ለዜጎች የቀረበው አገልግሎት አካል ነው። አገልግሎቱም ለ “ክላሊት” ደንበኞች ወዲያውኑ የሚቀርብ ሲሆን፣ ምንም አይነት ምዝገባ አያስፈልግም።
የሕጉ ጥቅም ምንድነው?
ሕጉ እንደ አጠቃላይ በጤናው መስክ በተለይ ደግሞ በአፍ እና በጥርስ ጤና ላይ ተጨባጭ አብዮትን የፈጠረ ነው። እስከ ከሁለት – ሶስት አስርተ ዓመታት ድረስ፣ የጥርስ ህክምና ይሰጥ የነበረው በግል ክሊኒኮች ነበር፣ ዋጋውም የአብዛኞችን ቤተሰቦች አቅም ያላገናዘበ ነበር፣ እና አንዳንዶቹ የልጆቻቸውን እና የራሳቸውን ጥርስ ችላ ለማለት ተገደው ነበር። ችግሩም በሀገሪቱ ጫንቃ ላይ የወደቀ ሸክም ሆነ — የጤና መጓደል ያለበት ጥርስ ያላቸው ጎልማሶች ከኢንፌክሽን ጋር በተያያዙ በሽታዎች የመታመም እና ሆስፒታል የመግባት ዕድላቸው የሰፋ ነው፤ ይኸውም ከስራ መቅረትን የሚያስከትል እና በጤና ስርዓቱ ላይ ሸክም የሆነ ነው። ልጆች ለረዥም ጊዜ ህክምና ሳያገኙ ይቆያሉ፣ እና ወደ ውትድርና ሲገቡ፣ የሚሊታሪ ሲስተሙ ለህክምና በዓመት 40 ሚሊዮን ILS ይደጉማል። ጥርሳቸውን ያጡ ጎልማሶች የሚደርስባቸው ስቃይ እና በህይወታቸው ላይ የሚያደርስባቸው ጉዳት ትልቅ ነው። ለዜጎች እኩልነት እና ለተሻለ ህይወት ለሚጨነቅ ማንኛውም ሰው፣ ይህንን ችግር በብሔራዊ ደረጃ መቅረፍ ጠቃሚ መሆኑ ግልፅ የሆነ ነገር ነው።
ለልጆች ነፃ የጥርስ ህክምና የሚሰጥ ሕግ፣ በሂደት የጤና፣ የኢኮኖሚ፣ እና የማህበራዊ ችግሮችን ይቀርፋል፣ እና በጎ አሻራውም በሀገሪቱ አጠቃላይ የጤና መስክ ላይ በመጪዎቹ አስርት ዓመታት የሚታይ ይሆናል። የብሩክዳል ኢንስቲቲዩት ተመራማሪዎች እንዳገኙት 64% ዜጎች ስለ ሕጉ ግንዛቤ አላቸው፣ እና የጤና ኢንሹራንስ ቡድኖች አገልግሎቶችን ይጠቀማሉ፣ ይኸውም በግንዛቤ ረገድ አስደናቂ ጭማሪ መኖሩን፣ እና አስፈላጊ እና ስኬታማ ሕግ መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።
ሕጉ ለልጆች የሚያቀርበው፣ እና የማያቀርበው ምንድነው?
የክላሊት አባላት ሁሉ 18 ዓመት (በ Gregorian ቀን መቁደር) እስከሚሞሉ ድረስ በጤና ጥበቃ סל ውስጥ ጥርስ ምርመራ ለማግኘት זכאים ናቸው. አገልግሎቶች סל አብዛኛውን ጥርስ ምርመራዎችን ያካትታል, ጥርስ ማስተካከያ (ኦርቶዶንቲክስ), ውበት ጥርስ ምርመራ እና ቋሚ ማደገኛ አለበለዚያ.
በጤና ጥቅል ውስጥ የተካተቱት የጥርስ ህክምናዎች የትኞቹ ናቸው?
በጥቅሉ ውስጥ በጣም የተለያዩ የጥርስ ህክምናዎች ተካትተዋል፣ አንዳንዶቹ በነፃ፣ እና ሌሎቹ ደግሞ በአነስተኛ የግል ተሳትፎ ነው።
የህክምና አይነት | የግል ተሳትፎ ክፍያ |
በየተወሰነ ጊዜ በጥርስ ሀኪም የሚደረግ ቼካፕ – በዓመት አንድ ጊዜ | ነፃ |
መደበኛ ህክምና እና ክትትል – የህክምና አካል እንደመሆኑ | ነፃ |
የማማከር እና ለህክምና ፕላን ዝግጅት – በዓመት አንድ ጊዜ | ነፃ |
ኤክስ-ሬይ – በህክምና ወቅት | ነፃ |
ጥንድ የንክሻ ፎቶዎች – በየተወሰነ ጊዜ በሚደረገው ቼካፕ ውስጥ ባለ መዋቅር | ነፃ |
የአፍ ንፅህና መምሪያ – በዓመት ውስጥ እስከ ሁለት ጊዜ። | ነፃ |
የወየቡ ጥርሶችን ማፅዳት – በዓመት አንድ ጊዜ | ነፃ |
ውሱን ስፍራ ላይ በቦታው የመከላከል ህክምና – (የፍሎራይድ ህክምና) | ነፃ |
ስንጥቅ እና ጥርስ ማሸግ | ነፃ |
የመጀመሪያ ደረጃ እርዳታ | ነፃ |
በአማልጋም እና ሌሎች ውህዶች ዳግም መገንባት (“የሙሌት ስራዎች”) | 27.69 ILS |
በወተት ጥርስ ውስጥ የዴንታል ፐልፕ ህክምና (የሩት ካናል ህክምናን ጨምሮ) | 27.69 ILS |
ለአጭር ጊዜ እና የጥርስ ናሙና ወይም ካስት መዋቅሮች | 27.69 ILS |
እንደ ህክምናው አስፈላጊነት – (ፕሪካስት ክራውን) | 27.69 ILS |
ጥርስ መንቀል በቀዶ ህክምና መንቀልን ጨምሮ | 27.69 ILS |
ከጥርስ ነቀላ በኋላ ክፍተቱን ማስጠበቅ | 27.69 ILS |
ላፊንግ ጋዝ ወይም ማደንዘዣ መጠቀም | 27.69 ILS |
በልጅነታቸው የጥርስ መበስበስ ላጋጠማቸው፣ እስከ 5 ዓመት ዕድሜ ላላቸው ህፃናት ማደንዘዣ። | ፍርይ |
ህክምናዎቹ የሚሰጡት በ “ክላሊት ስማይል” ክሊኒኮች እና ከ “ክላሊት ስማይል” ጋር ስምምነት ባላቸው የግል ክሊኒኮች ውስጥ ነው – ክሊኒኮችን ለመፈለግ፣ እዚህ ጋር ይጫኑ።
የግል ተሳትፎን የተመለከቱ ወጪዎች ከጤና ሚንስትር የምንቀበላቸውን ትዕዛዛት ባማከለ መልኩ ሊለወጡ የሚችሉ ናቸው።
የግል ተሳትፎ ወጭ ምንድነው?
እንደተገለፀው፣ ለልጅዎ የሚሰጡ አብዛኛዎቹ ህክምናዎች ነፃ ናቸው። የግል ተሳትፎን በሚጠይቁ የጥርስ ህክምናዎች ላይ፣ የክፍያ ጣሪያው 27.69 ILS ነው። የግል ተሳትፎን በሚጠይቅ በአንድ የህክምና ቆይታ ወቅት ከአንድ በላይ ህክምና የሚያስፈልግ ከሆነ፣ በዚያ የህክምና ቆይታ ውስጥ የግል ተሳትፎ ከፍተኛው የክፍያ ጣሪያ 55.39 ILS ነው።
“ክላሊት ስማይል” አገልግሎቱን ተደራሽ የሚያደርገው እንዴት ነው?
"ክላሊት" የጥርስ ህክምናን በ "ክላሊት ስማይል" የጥርስ ክሊኒኮች በኩል ተደራሽ በማድረግ ግንባር ቀደሙ ነው። በተጨማሪም፣ አዳዲስ ክሊኒኮች ተጨምረዋል፣ እና በነባር ክሊኒኮች ደግሞ ለልጆች ተስማሚ በሆነ መልኩ መዋቅራዊ እና ሌሎች ለውጦች ተደርገዋል። የዚህ አካል በሆነ መልኩ፣ ክሊኒኮቹ ለልጆች "አመቺ" ሆነዋል – ልዩ የህክምና ክፍሎች፣ የመቆያ ስፍራዎች፣ እንዲሁም የመጫዎቻ ቦታዎች፣ እና በአንዳንድ ቦታዎች ደግሞ፣ የልጆች ብቻ ክሊኒኮች ተቋቁመዋል። በተጨማሪም፣ ለህክምና ባለሙያዎቹ የመረጃ እና የጥናት ቀናት ይዘጋጃል፣ ይኸውም የጥርስ ሀኪሞቹ ለልጆች ልዩ ስለሆኑ የሜዲካል እና ፊዚዮሎጂካል የህክምና ስልቶች ላይ ወቅቱን የጠበቀ ግንዛቤን ለማስጨበጥ ነው።
አገልግሎቱ የሚሰጠው የት ነው እና ቀጠሮ የሚያዘውስ እንዴት ነው?
አገልግሎቱ በመላው ሀገሪቱ በተሰራጩት እያንዳንዱ የ "ክላሊት ስማይል" 107 ክሊኒኮች የቀረበ ነው። በተጨማሪም፣ ከሌሎች የግል የጥርስ ክሊኒኮች ጋር የኮንትራት ስምምነት ተፈራርመናል ይኸውም ወጣ ባሉ አካባቢዎች፣ በአረብ ሴክተር መንደሮች፣ እና ኦርቶዶክስ ሠፈራዎች አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው።
ህክምናው እንዴት ነው የሚዘጋጀው?
በ WhatsApp መልዕክት ይላኩልን
በድረ-ገፅ፤ በድረገፃችን ላይ ወይም በ “ክላሊት” አፕሊኬሽን ከጥርስ ሐኪሙ ጋር ቀጠሮ ያስይዙ
በስልክ፡ እርስዎ ማግኘት የፈለጉትን የህክምና አይነት መሰረት አድርገው “ክላሊት ስማይል” ክሊኒኮችን ይጎብኙ
የጥርስ ሐኪም መምረጥ እችላለሁ?
በሚገባ! የጥርስ ሐኪምዎን በእያንዳንዱ የ “ክላሊት ስማይል” ክሊኒኮች መምረጥ ይችላሉ፣ ወይም ከ “ክላሊት” ጋር ስምምነት ባላቸው ክሊኒኮች ውስጥም መምረጥ ይችላሉ።
በግል ህክምና ካደረግኹኝ፣ የገንዘብ ተመላሽ ይደረግልኛል?
በህጉ መሰረት፣ በጤና ኢንሹራንስ አካላት በኩል ላልተደረጉ፣ በግል ለተደረገ ህክምና ምንም የገንዘብ ተመላሽ አይሰጥም።
כללית סמייל