חיפוש נותני שירות ברשת כללית סמייל

יש לבחור את קטגוריית החיפוש הרצויה

דף הבית>አስቸኳይ የጥርስ ህክምና–እንዲታወቅ አስፈላጊ የሚሆነው ምንድን ነው ;

አስቸኳይ የጥርስ ህክምና–እንዲታወቅ አስፈላጊ የሚሆነው ምንድን ነው ;

የጥርስ አስቸኳይ ህክምና በህክምና ጣቢያ ስማየል ክላሊት ሁሉ በስራ ስኣቶች

 ይሰጣል ፡፡

ወደ ህክምና ጣቢያው ከመድረሳቹሁ በፊት ስልክ መደውል እስፈላጊ ነው፡፡

የህክምና ባለ ሚያዎች በተቻለ መጠን በአስአኳይ ያክሙሃል፡፡ ማለትም

 ቀድመው ተራ የያዙ ከመታከማቸው በኃላ፡፡

የህክመናው ጣቢያ ተዘግቷዋልን ?ተዘግቶ ከሆነ ወደ ኣንዱ ሌላ የኣስቸኳይ የህክምና ጣቢያ መሄድ ይቻላል ፡፡

የህክምናው ክፍያ ዋጋ ህክምናው ካለቀ በኋላ ብቻ ነው መታወቅ የሚቻለው፡፡

ያም ሆነ ይህ ለቀጣይ ህክምናና ምርመራ ተራ መያዝ

 እኛ ለአንተ ሲባል እዚህ አለነልህ

ለጥርስ ህክምና እና የጥርስ ድንገተኛ ጉዳት “ክላሊት ስማይል” አለላችሁ።

በእያንዳንዱ የስማይል ክሊኒክ የሚገኙ የህክምና ቡድኖች በሚገባ የሰለጠኑ ሲሆኑ በማንኛውም የስራ ሰዐት ፤ ከጥርስ ጋር ለተያያዙ ህክምናዎች የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና እርዳታ ለማድረግ ተዘጋጅተው የሚጠብቁ ናቸው።

ከመምጣታችሁ በፊት ወደ ክሊኒኩ ስልክ መደወላችሁ ጠቃሚ ነው። ይኅውም እናንተ ከመምጣታችሁ በፊት የህክምና ቡድኑ ተዘጋጅቶ እንዲጠብቅ እና፤ አንዳንድጊዜም የስራ ጫና በሚኖርበት ወቅት እናንተን ወረፋ ላለማስጠበቅ ወይም እናንተ የፈለጋችሁት የህክምና አይነት በተቋሙ የማይሰጥ ከሆነ፣ ወደ ሌላ የህክምና ተቋም እንድትመሩ አመቺ ሁኔታን ይፈጥራል።

በጥርስ ላይ ጉዳት የደረሰባቸው የ “ክላሊት ሄልዝ ሰርቪስ” ታካሚዎች የመጀመሪያ የህክምና እርዳታ የሚሰጣቸው ልጆች እስከ 18 አመታቸው ድረስ በልጆች የአገልግሎት ፓኬጅ በተገለፀው መሰረት ከ “ክላሊት ስማይል ክሊኒክ” እና ከመጀመሪያ የህክምና እርዳታ ማዕከላት ነው። በፓኬጅ አገልግሎቱ ላይ ያልተገለፁ ህክምናዎች፣ በደንቡ መሰረት ክፍያ ከፍላችሁ የምታገኟቸው ናቸው።

የመደበኛ የትምህርት ስርዐቱ (ከ3 አመት እስከ 18 አመት) ተማሪ ጥርስ ላይ ለደረሰ ጉዳት የገንዘብ ተመላሽ ለማግኘት፣ በ “ኢንባል ኢንሹራንስ” አማካኝነት ትምህርት ሚኒስተርን ማሳወቅ ይቻላል። ለተጨማሪ መረጃ – http://cms.education.gov.il/EducationCMS/Units/bituach/NifgaeTeuna/dental+treatment.htm

የመንጋጭላ አጥንት የተሰነጠቀ ከመሰላችሁ፤ የአፍ እና የማክሲሎፋሲያል የቀዶ ጥገና ህክምና ክፍል ወደሚገኝበት የሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል መሄድ አለባችሁ።

በስሜትና በሞያነት

ወደ የጥርስ ህክምና ስማይል ክላሊት ስትደርስ የህክማና ባለሞያዎች ታካሚዎች እያከሙ መሆናቸው ብታውቅ ይመረጣል ፤ ስለሆነ ከሃኪሞቹ አንዱ ስራው አብቅቶ ወደ አንተ መጥቶ እስኪመረምርህ ድረስ ትእግስት እንድታደርግ ልትጠየቅ ትችላለህ በትእግስት ተጠባበቅ፡፡

አንድ አንድ ጊዜ ባንድ ጊዜ አስቸኳይ ህክምና የሚስፈልጋቸው ታካሚዎች ወደ ህክምና ጣቢያው ባንድ ላይ ይደርሳሉ፡፡ከዚህም በተጨማሪ አበረውህ ወረፋ ይዘው ከሚጠብቁት ውስጥ ለወራት ያህል ቀድመው ወረፋ የያዙ እንደሚገኙባቸው እወቅ፡፡ እንደነዚህ ለመሳሰሉትም ደረጃው ክፍ የለና ተወዳዳሪ የለለው የህክምና እንክብካቤ የማድረግ ግዴታ አለብን፡፡

የሌሎች ታካሚዎች አስቸኳይና ሞያተኛ ህክምና የመቀበል መብታቸው ሳይጓደል ለአንተም በተቻለ መጠን አስቸኳይ ህክምና ለመስጠት የህክምና ጣቢያው ቡድን የተቻለውን ያህል ጥረት እያደረገ ነው፡፡

ከተለመደው የስራ ሳኣት ውጭ በጥርስ ህክምና ጣቢያ አስቸኳይ ህክምና ማድረግ በሚያስፍልግበት ወቅት ከአስቸኳይ የህክምና ጣቢያዎቹ ወደ አንዱ መሄድ ይቻላል፡፡ ደርሶ ረዢም ጊዜ ከመጠበቅ ለመቆጠብ ያህል እስቀድሞ ወረፋ መያዝ ይመረጣል፡፡

የጥርስ አስቸኳይ ህክምና ስንት ያስከፍላል;

በመጀመሪያው ህክምና የታካሚው ሁኔታ በትክክል ማወቅ ስልማይቻል የጥርስ አስቸኳይ ህክምና ክፍያ ከመታከም በፊት አስቀድሞ መወሰን አይቻልም፡፡ይህም የሆነው የአስቸኳይ ህክማና ባሃሬ በመታከሙ ሄደት ላይ አስቀድሞ ማወቅ የማይቻል የመጎዳትና የጉዳት ችግሮች ነው፡፡

ስለሆነ የጥርስ የአስቸኳይ ህክምና ክፍያ የታካሚው ሁኔታ ከታወቀና ህክምናው ከበቃ በሁዋላ ነው የሚታወቀው፡፡

በቀጣይነት መታከሙ ጥቅሙ ምንድን ነው;

የጥርስ አስቸኳይ ህክምና አላማ የጥርሱ ሁኔታ መባባሱ መግታትና ማመሙ በአስቸኳይ መግታት መሆኑ ማወቁ አስፈላጊ ነው፡፡ ቢሆንም የዚህ አይነት ህክምና ለተከሰተው የጥርስ ህመም ሙሉና ሞያዊ ምላሽ መስጠት አይችልም፡፡ በተጨማሪም የሚደረገልህ ህክምና ቅጽበታዊ ምላሹ ላይሰጥ ይችላል ፤ ስለሆነ ህክምናው እስኪያድንህ ድረስ ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ሊሆን ይችላል፡፡

ያም ሆነ ይህ አስቸኳይ ህክምና ከተደረገልህ በሁዋላ ለቀጣዩ ህክምናህ ቀጠሮ መያዝ አስፈላጊ ሲሆም እንዲያውም ግዴታም ነው፡፡ ስለሆነ ፡ በንደዚህ ያለ ሁኔታ የክላሊት ስማይል የህክማና ቡድኑ ሁሉም ያካተተ ፡ መሰረታዊና ሞያዊ ህክማና ሊያድርግልህ ይችላል፡፡ በቀጣይነት አለመታከሙ ለተጎዳው ቦታ ባቻ ሳይሆን አጠገቡ (ጥጉ ላይ) ለሚገኙት እና ለጥርስ ስርም ጭምር ጉዳት ሊስከትል ይችላል፡፡

ተሎ ጤናህ አጊነተህ እንድትድን እንመኝልህ አለን!

כללית סמייל

רפואת שיניים מקצוענית