חיפוש נותני שירות ברשת כללית סמייל

יש לבחור את קטגוריית החיפוש הרצויה

דף הבית>ለ ኦንኮሎጂ ታካሚዎች የጥርስ ህክምና – ማወቅ የሚያስፈልጋችሁ ሁሉም ነገር

ለ ኦንኮሎጂ ታካሚዎች የጥርስ ህክምና – ማወቅ የሚያስፈልጋችሁ ሁሉም ነገር

ካንሰር በዓለም ውስጥ በጣም የተለመደ በሽታ አጠቃላይ መጠሪያ ስም ነው። የጤና ሚኒስቴር ዳታ እንድደሚያሳየው በእስራዔል ውስጥ በየዓመቱ፣ 30000 አዳዲስ የካንሰር ኬዞች በምርመራ ይለያሉ። ከ200 በላይ የተለያዩ አይነት የካንሰር ዓይነቶች አሉ፣ እነዚህም ሠውነትን በተለያየ መንገድ ያጠቃሉ፣ እያንዳንዳቸውን ለመቋቋም እና ለመታከምም የተለያየ መንገድ አላቸው። አንዳንድ በሽተኞች ከበሽታው ጋር የሚያደርጉትን ትግል ወደ ህይወታቸው ማዕከል ለማስገባት ይገደዳሉ፣ አንዳንዶች ደግሞ ከህክምናቸው ጋር የዕለት ተዕለት ህይወታቸውን በመቀጠል ተሳክቶላቸዋል። አንድ ነገር ግን እርግጥ ነው፣ ሁሉም ቢሆኑ ከዚህ በፊት የማያውቁትን ሁኔታ መቋቋም አለባቸው።

እኛ “Clalit” በእነዚህ አስቸጋሪ ጊዜያት ታካሚዎችን በመደገፍ እንቆማለን እናም ለመርዳት እንፈልጋለን። በበሽታው እና በማገገም ወቅት፣ ታካሚዎች በጣም ብዙ ጥያቄዎች ሊያጋጥሟቸው ይችላል እና በተቻለ መጠን በሁሉም ዘርፍ ተደራሽ መረጃ ያስፈልጋቸዋል። እናም በሽተኞች በተመቻቸ ሁኔታ ህክምናቸውን እና የማገገሚያ ጊዜያቸውን በትንሹም ቢሆን እንዲያጠናቅቁ ለመርዳት፣ ከሀገሪቱ እንዲሁም ከ እኛ “ከክላሊቶች” ድጋፍ ለሚገባቸው ታካሚዎች የአፍ እና የጥርስ ክብካቤን በተመለከተ አጭር እና ጥልቅ መረጃዎችን የያዘ መምሪያ አዘጋጅተናል።

እዚህ ጋር የቀረበው አብዛኛው መረጃ የኦንኮሎጂ ታካሚ እንደሆኑ በምርመራ ለተለዩት የ “Clalit” ደንበኞቻችን ታትሞ ከተሰጣቸው ብሮሸር ውስጥ ተካትቷል፣ በተጨማሪም፣ ዝርዝር የቀረበው መረጃ በ “Clalit” ድረ ገፅ ላይ “ለኦንኮሎጂ ታካሚዎች ሙሉ መምሪያ” በሚለው ውስጥ ይገኛል፣ ይህም እዚህ ጋ ይገኛል።

የሚገባችሁን የገንዘብ ተመላሽ የማግኘት ሂደትን በተመለከተ፣ እና ለኦንኮሎጂ ታካሚ ቅፁን/ፎርሙን ዳውንሎድ ለማድረግ እባክዎ ሪፖርቱን እስከ መጨረሻ ድረስ ማንበብዎን ይቀጥሉ።

ለኦንኮሎጂ ታካሚ ከ ኬሞቴራፒ ወይም ከጨረር ህክምና በፊት የጥርስ ህክምና

የኬሞቴራፒ ወይም የጨረር ህክምና ከማድረጋቸው በፊት ታካሚዎች አንዳንድ ጊዜ የጥርስ ማገገሚያ ወይም ማቆያ ለማድረግ ይገደዳሉ። እነዚህ ታካሚዎች የኦንኮሎጂ በሽታ ምርመራ ከተደረገላቸው ቀን እስከ ኬሞቴራፒ ወይም የጨረር ህክምና እስከሚጀምሩበት ቀን ድረስ ለሚደረግላቸው የጥርስ ህክምና የገንዘብ ተመላሽ የመቀበል መብቱ አላቸው።

የሚከተሉት የህክምና አይነቶች የገንዘብ ተመላሽ መጠየቅ የምትችሉባቸው የህክምና አይነቶች ናቸው፤

  • የማቆያ ህክምናዎች እነዚህም ከሚያካትቱት ውስጥ የወየቡ ጥርሶችን ማንፃት፣ ሙሌት፣ መንቀል፣ ኤክስ-ሬይ እና ሌሎችም..
  • የማገገሚያ ህክምናዎች እነዚህም ከሚያካትቱት ውስጥ የ ሪሲን ዴንቸር እና ክራውን (ጊዜያዊ አክሬሊክ ክራውን)፣ ነገር ግን የ ፖርሲሊን ክራውኖችን አያካትትም።

የገንዘብ ተመላሹ ምን ያህል ነው፣ እና ህክምናው የት መደረግ ይችላል?

  • ህክምናውን በ “Clalit Smile” ክሊኒኮች ማግኘት ይቻላል፣ እና በባስኬት ውስጥ ለተካተቱ ህክምናዎች በዋጋ ዝርዝሩ ላይ የ 50% ቅናሽ ከ “Clalit Smile” ያገኛሉ።
  • እንደ አማራጭም፣ ህክምናዎችን በግል መታከም እና የ 50% የገንዘብ ተመላሹን ከ “Clalit” በህክምና ታሪፉ ታገኛላችሁ።
  • አንድ ታካሚ የጥርስ ህክምናውን በህዝብ ሆስፒታል ካከናወነ፣ የትክክለኛ ዋጋውን 50% የገንዘብ ተመላሽ የማግኘት መብት አለው፣ እና ከጤና ሚኒስቴር ታሪፍ የበለጠ አይሆንም።

የገንዘብ ተመላሽ ለመቀበል፣ ስለ በሽታው የሚገልፅ ሀተታ፣ የጥርስ ህክምና ፕላን፣ በ “Clalit” ሰርቲፋይድ ሐኪም ማረጋገጫ እና ኦሪጅናል የ ታክስ ኢንቮይስ ደረሰኝ፣ ወይም ኦሪጅናል ደረሰኝ በመያዝ በ “Clalit” እናት ክሊኒኮች ላይ ማመልከት ይቻላል።

ከኬሞቴራፒ ወይም ከራዲየሽን ህክምና በኋላ ለታካሚዎች የጥርስ ህክምና

  • በዚህ ጉዳይ የኦንኮሎጂ ታካሚው ከኬሞቴራፒ ወይም ከራዲየሽን ህክምና በኋላ በሪሲን የማቆየት ወይም የማገገሚያ ህክምና የሚሰጠው ይሆናል።
  • የማቆያ ህክምና የ ኤክስ-ሬይ፣ የመንቀል፣ የሙሌት፣ የወየቡ ጥርሶችን ማፅዳት ያካትታል።
  • የማገገሚያ ህክምና የሪሲን ዴንቸር እና ክራውን (ጊዜያዊ አክሬሊክ ክራውን) የሚያካትት ሲሆን፣ ነገር ግን ፕሮስሊን ክራውን አያካትትም።

የገንዘብ ተመላሹ ምን ያህል ነው፣ እና ህክምናውን የት ማድረግ ይቻላል?

ሁሉንም ህክምናዎች በ “Clalit Smile” ክሊኒኮች ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በ ባስኬት ውስጥ ለተካተቱት ህክምናዎች 100% የገንዘብ ተመላሽ ይደረጋል፣ (በ ባስኬት ውስጥ ላልተካተቱት ህክምናዎች በክፍያ አገልግሎት ይሰጣችኋል)

እንደ አማራጭም፣ ህክምናዎችን በግል በማግኘት 100% የገንዘብ ተመላሹን ከ “Clalit” በህክምና ታሪፍ መቀበል ትችላላችሁ።

አንድ ታካሚ የጥርስ ህክምናውን በህዝብ ሆስፒታል ካከናወነ፣ የትክክለኛ ዋጋውን 50% የገንዘብ ተመላሽ የማግኘት መብት አለው፣ እና ከጤና ሚኒስቴር ታሪፍ የበለጠ አይሆንም።

የጥርስ ህክምና እና ከ ቢስፎስፌኔት ወይም ዲኖሱማብ ህክምና በፊት የገንዘብ ተመላሽ

በ ኮመን ማይሎማ ወይም በአጥንት ሜታስታሲስ ምክንያት ለኦንኮሎጂ ታካሚዎች ከ ቢስፎስፌኔት ወይም ከ ዲኖሱማብ ህክምና በፊት የመከላከያ የጥርስ ህክምናዎች፣ የማቆያ እና የማገገሚያ (የቅድመ ህክምና ብቻ)  የሚሰጥ ይሆናል።

ሁሉንም ህክምናዎች ከ “Clalit Smile” ክሊኒኮች ማግኘት የሚችሉ ሲሆን በባስኬት ውስጥ ለተካተቱ ህክምናወች ከ “Clalit Smile” የዋጋ ዝርዝር የ 50% ቅናሽ ያገኛሉ። እንደ አማራጭም፣ ህክምናዎችን በግል በማግኘት 50% የገንዘብ ተመላሹን ከ “Clalit” ህክምና ታሪፍ ታገኛላችሁ።

ታካሚው የጥርስ ህክምናውን ያከናወነው በ “Clalit” ሆስፒታል ወይም በህዝብ ሆስፒታል ከሆነ፣ የትክክለኛ ዋጋውን 50% የገንዘብ ተመላሽ የማግኘት መብት አለው፣ እና ከጤና ሚኒስቴር ታሪፍ የበለጠ አይሆንም።

ለገንዘብ ተመላሽ እንዴት ነው የማመለክተው?

የገንዘብ ተመላሽ ለመቀበል፣ ስለ በሽታው የሚገልፅ ሀተታ፣ የጥርስ ህክምና ፕላን፣ በ “Clalit” ሰርቲፋይድ ሐኪም ማረጋገጫ እና ኦሪጅናል የ ታክስ ኢንቮይስ ደረሰኝ፣ ወይም ኦሪጅናል ደረሰኝ በመያዝ በ “Clalit” እናት ክሊኒኮች ላይ ማመልከት ይቻላል።

የኦንኮሎጂ ታካሚ ቅፅ/ፎርም

እናንተ ባለመብት የሆናችሁበትን የገንዘብ ተመላሽ ለመቀበል፣ የጥርስ ህክምናውን ከመጀመራችሁ በፊት ወደ ኦንኮሎጂስታችሁ ብትሄዱ ጠቃሚ ነው፣ እናም በ “Clalit Smile” የኦንኮሎጂ ታካሚ ቅፅ ላይ ያሉ ዝርዝሮችን እንዲሞላላችሁ ጠይቁት – ቅፁን ዳውንሎድ ለማድረግ ይህን ይጫኑ። 

ወደ ክሊኒክ ስትመጡ፣ የተሟላውን ቅፅ ለክሊኒኩ መዝገብ ያዥ ማስገባት አለባችሁ። የጥርስ ሀኪሙ የክሊኒክ ምርመራ እና ኤክስ-ሬይ ካደረገ በኋላ (የአገልግሎት ባስኬት መምሪያዎችን ተከትሎ ታካሚው አገልግሎቱ ይገባዋል ወይስ አይገባውም የሚለው እስኪወሰን ድረስ ምርመራዎች በታካሚው ወጭ የሚደረጉ ይሆናል፣ እርስዎ የሚገባዎት ሆነው ከተገኙ፣ ለምርመራ እና ለ ኤክስ-ሬይ ያወጡት ወጪ ተመላሽ ይደረግልወታል)፣ የጥርስ ሀኪሙም ተገቢ ነው የሚለውን የህክምና ፕላን የሚያዘጋጅ ይሆናል

የህክምና ፕላኑም በአገልግሎት ባስኬት ላይ በተገለፁ ደንቦች መሰረት ባለመብትነቱን ለመገምገም ወደ ክሊኒኩ ቢሮ ይላካል። በባስኬት ውስጥ ለተካተቱ የጥርስ ህክምናዎች፣ ታካሚው ክፍያ አይጠየቅም። በጤና ባስኬቱ ውስጥ ላልተካተቱ የጥርስ ህክምናዎች፣ ታካሚው በ “Clalit Smile” ታሪፍ መሰረት ክፍያ የሚፈፅም ይሆናል (የክፍያ ታሪፎችን በተመለከተ ሙሉ መረጃ ለማግኘት ወደ ክሊኒኩ ቢሮ እንድትሄዱ እንመክራለን)

የበለጠ መረጃ እንዲሰጠኝ እፈልጋለሁ

እኛ “Clalit Smile” እና “Clalit” እንደ አጠቃላይ፣ ታካሚዎች በህክምናቸው እና በበሽታ አያያዛቸው ውስጥ በምንችለው አቅም ከኦንኮሎጂ ታካሚዎች ጎን ለመሆን ጥረት እናደርጋለን፤ ርዕሱን በተመለከተ አጥጋቢ መልስ እንዳላገኙ ከተሰማዎት፣ በ ኢሜይል እንዲያማክሩን እንጋብዝዎታለን፣ እንዲሁም በተቻለ መጠን ለመርዳት እንሞክራለን፤  [email protected]

እንዲሁም ደግሞ ወደ “Clalit” የመረጃ ማዕከል በስልክ ቁጥር *2700 ማመልከት ይችላሉ

כללית סמייל

רפואת שיניים מקצוענית