ለጎልማሶች የድጎማ የጥርስ ህክምና – ማወቅ ያለባችሁ ነገር
ዕድሜያቸው 72 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ጎልማሶች የሚሰጥ የጥርስ ህክምና ሪፎርም ከ ጁላይ 2022 ጀምሮ በስፋት ተተግብሯል፤ የትኞቹን የጥርስ ህክምናዎች ነው በነፃ ማግኘት የምንችለው? በየትኞቹ የጥርስ ህክምናዎች ነው የግል ተሳትፎ አስፈላጊ የሆነው? እና ምን ያህል ነው? እና ምርጥ የሆነውን የጥርስ ሐኪም ለራስዎ የሚመርጡት እንዴት ነው
የጎልማሶች ነፃ የጥርስ ህክምና ሪፎርም ምንድነው?
በጤና ጥቅሉ መሰረት ዕድሜያቸው 72 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ጎልማሶች በአነስተኛ የግል ተሳትፎ የሚሰጠው የጥርስ ህክምና ለብዙዎች መልካም ዜና ሆኗል እና የብዙዎችን ህይወት የሚቀይር እንዲሁም ጤናቸውንም የሚያስጠብቅ ነው እንዲሁም በራስ መተማመናቸውን መልሶ የሚያስገኝላቸው እና ህይወትንም በቀድሞ አኳኋን መቀጠል የሚያስችል ነው።
ሪፎርሙ ተግባር ላይ ከዋለ ከሶስት ዓመታት ወዲህ፣ ሀገሪቱ የታካሚዎችን መብት እንደገና ለማደስ ወስናለች፣ እና አሁን፣ ከ ጁላይ 1፣ 2022 ጀምሮ ዕድሜያቸው 72 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሁሉም ጎልማሶች ሙሉ የጥርስ ህክምና የሚያገኙ ይሆናል፣ የማቆየት እና የማገገሚያ፣ በጤና ጥቅሉ ተካትተዋል፣ እና እነዚያም ከዚህ በታች ባለው ሠንጠረዥ ተዘርዝረዋል።
በአግባቡ ህክምና ያላገኘ ጥርስ የአንድን ግለሰብ አሁናዊ ህይወት የሚያውክ እና እንደ አጠቃላይ የጤና ጉዳት የሚያስከትል ነው። የጥርስ ጤና ከፍተኛ ተፅዕኖ ያለው ነው፣ ይኸውም በጤናችን ላይ ብቻ ሳይሆን፣ በአኗኗራችን እና በክብራችን ላይ ጭምር ከፍተኛ ተፅዕኖ ያለው ነው።
እንዳለመታደል፣ ከ ታኡብ ኢንስቲዩት በ ዶ/ር ሆረቭ በተደረገ ምርምር፣ እስከ 40% የሚደርሱ ምላሽ ሰጪዎች ባለፈው ዓመት የጥርስ ህክምናቸውን የኢኮኖሚ አቅማቸውን ከግምት በማስገባት ህክምናቸውን ለመተው እንደተገደዱ መልስ ሰጥተዋል። አብዛኞቹ ጎልማሶች የጥርስ ህክምና ወጪዎችን የመሸፈን አቅሙ የላቸውም፣ እና በዚህ ምክንያት፣ ጥርሳቸውን ያጣሉ – ይኸውም ብዙ አይነት ምግቦችን መብላት ሊከልክላቸው ይችላል፣ እናም ደግሞ የአፍ እና የፊት መጣመምን ያስከትላል፣ ከዚያም አልፎ ለራሳቸው ያላቸውን ምልከታም ይጎዳል።
የህክምና ዝርዝሮች
ስለዚህ፣ ጎልማሶች በነፃ ሊያገኟቸው የሚችሉ የጥርስ ህክምናዎች የትኞቹ ናቸው? በግል ተሳትፎ የሚደረግባቸውስ የትኞቹ ናቸው፣ እና ክፍያውስ ምን ያህል ነው?
በጤና ጥቅሉ ውስጥ ዕድሜያቸው 72 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ጎልማሶች የጥርስ ህክምናን ማስቀጠል – ከጁላይ 1፣ 2022 ጀምሮ
ህክምና | ዝርዝር/አስተያየት | የግል ተሳትፎ ክፍያ |
የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ (የድንገተኛ ህክምና) | ለማዘግየት የማይቻል አስቸኳይ ህክምና፣ እንደ ማስታገሻ፣ የመድሀኒት ማዘዣ ወይም በከፍተኛ ኢንፌክሽን ሁኔታ ውስጥ የቀዶ ህክምና የመሳሰሉ። | 72.62 ILS |
በየተወሰነ ጊዜ በጥርስ ሀኪም መታየት | ማማከርን እና የህክምና ፕላን ዝግጅትን ጨምሮ በዓመት አንድ ጊዜ | ነፃ |
መደበኛ ምርመራ እና ክትትል | የህክምናው አካል እንደመሆኑ | ነፃ |
የ ንክሻ ፎቶግራፍ | በየተወሰነ ጊዜ በሚደረገው የምርመራ ጊዜ ውስጥ የሚደረግ ጥንድ የ ንክሻ ፎቶግራፎች | ነፃ |
የመለያ ፎቶግራፍ | በሁለት ዓመት አንዴ፣ የህክምናው አካል እንደመሆኑ | በ ፎቶ 36.40 ILS |
ፓኖራሚክ ፎቶግራፍ | በሁለት ዓመት አንዴ፣ የህክምናው አካል እንደመሆኑ | በ ፎቶ 36.40 ILS |
የወየቡ ጥርሶችን ማንፃት (የጥርስ ህክምና ድጋፍ) | በአንድ ዓመት ውስጥ ሁለት ጊዜ | ነፃ |
የፍሎራይድ ህክምና | በዓመት አንድ ጊዜ ፍሎራይድ ባለበት ውሱን ስፍራ ፍሎራይድ ላከር በመጠቀም | 18.15 ILS |
መንቀል | 36.40 ILS | |
በቀዶ ህክምና መንቀል ከጥርስ ሩት(ስር) ላይ መለያየት | 72.62 ILS | |
የ ሩት ህክምና ዕድሳት ወይም ህክምና | 145.25 ILS | |
የጥርስን ጫፍ መቁረጥ | ኤፒሰክትሚ | 145.25 ILS |
የጥርስ ዳግም ግንባታ (ሙሌት) | በአማልጋም ወይም በልይ ውህድ ቁስ ዳግም ግንባታ | 36.40 ILS |
Iፋስት ስትራክቸር | ከ ሩት ህክምና ወይም ከ ሩት ህክምና ዕድሳት በኋላ የጥርስ ማሟላት | 36.40 ILS |
ሩት ፕላኒንግ | የ ሩብ አፍ ህክምና (ለእያንዳንዱ የአፍ ሩብ በሁለት ዓመት አንዴ) | 108.93 ILS |
Tየማገገሚያ ህክምና ሠንጠረዥ
ህክምና | ዝርዝር/አስተያየት | የግል ተሳትፎ ክፍያ |
የአጭር ጊዜ ዴንቸር (አርቴፊሻል ጥርስ) | ለአጭር ጊዜ ለሚደረጉ ዴንቸሮች ዝግጅት ሙሉ እና ከፊል (የላይ እና የታች) ልኬታ እና ገጠማን ያካትታል | 217.87 ILS |
ለመንጋጋ ከፊል ዴንቸር (አርቴፊሻል ጥርስ) | ለእያንዳንዱ 4 ዓመታት ለእያንዳንዱ መንጋጋ ከ አንድ ዴንቸር አይበልጥም፣ ሆኖም ከመንጋጋ ውስጥ አንድ ብቻ ሞላር(ዊዝደም ቲዝ ሳይካተት) ከወለቀ በስተቀር ነው በላብራቶሪ ማምረት፣ መለካት፣ እና መግጠምን ያካትታል. |
326.81 ILS |
ለመንጋጋ ሙሉ ዴንቸር (አርቴፊሻል ጥርስ) | ሙሉ የላይ ወይም የታች ዴንቸር – ልኬታ፣ ገጠማ፣ በላብራቶሪ ማምረትን ያካትታል። በየ 7 ዓመቱ አንዴ ለእያንዳንዱ መንጋጋ አንድ ዴንቸር ይዘጋጃል | 326.81 ILS |
በክሊኒኩ ውስጥ ለሚከወን የዴንቸር (አርቴፊሻል ጥርስ) ገጠማ እና ፕሬዠር ፖይንት ለማስወገድ ወደ ጥርስ ሀኪም ለህክምና የሚያደርጉት ጉብኝት |
|
36.40 ILS |
ለሙሉ ዴንቸር ሶፍት እና ሃርድ ሽፋን | ሙሉ ዴንቸር ከተቀበሉ በኋላ በእያንዳንዱ ሰባት ዓመት እስከ 2 ጊዜ ሶፍት ወይም ሃርድ ሽፋን (በክሊኒክ ውስጥ ወይም በላብራቶሪ)። ሙሉ ዴንቸር ከተቀበሉ በኋላ በእያንዳንዱ ሰባት ዓመት እስከ ሶስት ጊዜ ሶፍት/ጊዜያዊ ሽፋን (በክሊኒክ ውስጥ) |
72.62 ILS |
ለሙሉ ዴንቸር የ መደብ ዕድሳት | ዴንቸሩን ከተቀበሉ በኋላ በእያንዳንዱ ሰባት ዓመት እስከ አንድ ጊዜ የዴንቸሩን መደብ በላብራቶሪ ውስጥ ማደስ እና መግጠም | 72.62 ILS |
ስንጥቅ መጠገን እና/ወይም ለዴንቸሩ ጥርስ መጨመር | ሙሉ ዴንቸር ከተቀበላችሁ በኋላ በእያንዳንዱ 7 ዓመት እስከ አንድ ጊዜ፣ ወይም ከፊል ዴንቸር ከተቀበላችሁ በኋላ በእያንዳንዱ 4 ዓመት አንድ ጊዜ | 36.40 ILS |
ለታችኛው ዴንቸር ኢምፕላንቶች | ሙሉ የታችኛውን ዴንቸር ለመደገፍ እስከ 4 ኢምፕላንቶችን መትከትል – ብቻ፣ የሚቻል ከሆነ፣ ያለ የዝግጅት ህክምና (በዚህ ጥቅል ውስጥ አልተካተተም) ለምርመራው ሲቲ ስካን ያስፈልጋል፣ ይኸውም በሌላ ተናጠል የግል ተሳትፎ በሚደረግ 34.54 ILS | በ ኢምፕላንት 108.93 ILS |
በሁለቱ ኢምፕላንቶች ላይ ለዴንቸሩ አገናኝ | ለ ኳስ መሰል ኮኔክተሮች ወይም ሎኬተርስ ምትክ – እንደ አስፈላጊነቱ በየሁለት ዓመቱ አንድ ጊዜ | 36.40 ILS |
ለኮኔክተሩ ረበር ባንድ | ለኳስ መሰል ኮኔክተሩ ወይም ሎኬተሩ የ ረበር ባንድ ምትክ – እንደ አስፈላጊነቱ በየስድስት ወሩ አንድ ጊዜ | 36.40 ILS |
ሩት ደን | ከዴንቸር ስር የተቆረጠ ሩት በላብራቶሪ ዳግም ግንባታ | 108.93 ILS |
ቬስቲቡሉምን ጥልቅ ማድረግ | በከንፈር እና በድድ መካከል ያለውን ስፍራ ለዴንቸሩ በሚሆን መልኩ በቀዶ ጥገና ጥልቅ ማድረግ | 36.40 ILS |
ቫልቩሎፕላስቲ ፐርፎርማንስ | በዴንቸሩ ስር ያለውን ቅርፊተ አጥንት ማለዘብ | 36.40 ILS |
የጥርስ ዘውድ | ለከፊል ዲንቸር ብቻ እንደ ደጋፊ የሚሆን ዘውድ፣ በዴንቸር እስከ ሶስት ዘውድ | 217.87 ILS |
- ለድንገተኛ ህክምና ከባድ የ ጀሪያትሪክ ፔሸንቶችን ማጓጓዝ
- ለፕሮስቴቲክ ህክምና ከ 3 ወራት በላይ ሆስፒታል ውስጥ የተኙ ከባድ የ ጀሪያትሪክ ፔሸንቶችን ማጓጓዝ
አንድ ሰው በአዲሱ ማሻሻያ መሰረት የጥርስ ህክምናውን የት እንደሚያደርግ እንዴት ሊወስን ይችላል? ያው ለሁሉም የታወቀ እንደመሆኑ፣ በጥርስ ቀልድ የለም፣ እናም የተለያዩ የጥርስ ሀኪሞች ያላቸው የሙያ ብቃትም ደረጃም በእጅጉ የተለያየ ነው። የተሳሳተ ምርመራ፣ እንዲሁም የችኮላ ወይም የቸልታ የጥርስ ህክምና፣ ውጤቱ በአብዛኛው ከባድ ጉዳት እና ትልቅ ጭንቀት የሚያስከትል ነው።
ከሆሎኮስት (ከዘር ጭፍጨፋ) ለተረፉት ጥቅማጥቅሞች
ከ ኤፕሪል 2021 ጀምሮ፣ ከሆሎኮስት ለተረፉ እና ዕድሜያቸው 72 እና ከዚያ በላይ ለሆኑ የ “ክላሊት” መድህን ተጠቃሚዎች እንዲሁም በ ናዚ ማሰቃያዎች ምክንያት የታወቀ በሽታ ያለባቸው ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ለያዙ በሙሉ (እንዲሁም ከዘር ጭፍጨፋው የተረፉትን ያካትታል ይኸውም ከጀርመን ጡረታ የሚቀበሉ እና ለህክምና ወጪያቸውም የገንዘብ ድጋፍ የማግኘት መብት ላላቸው እና እንደ ከዘር ጭፍጨፋ የተረፉ እንደመሆናቸው ከገንዘብ ሚኒስተር ጡረታ የሚቀበሉ፣ ለዚህም በገንዘብ ሚኒስቴር ከዘር ጭፍጨዋ የተረፉት በባለስልጣኑ የተለየ የአካል ጉድለት ወይም ዲስኤቢሊቲ ካላቸው) በ “ክላሊት” የጤና ጥቅል ውስጥ የተካተቱትን የጥርስ ህክምና የግል ተሳትፎ ክፍያዎች ሳይከፍሉ ሙሉ ለሙሉ ነፃ አገልግሎት ያገኛሉ።
የ ዴንታል ኢምፕላንት በ ስፔሻሊስት የጥርስ ሐኪም
በእስራኤል፣ ከሁሉም ዴንቲስቶች ውስጥ ስፔሻሊስት ያደረጉት 8% ብቻ ሲሆን በ “ክላሊት” ውስጥ ግን፣ ከ 4ቱ የጥርስ ሐኪሞች 1ዱ ስፔሻሊስት ነው (24%)
ስለ ዴንታል ኢምፕላንቱ ማወቅ የሚያስፈልጋችሁ ነገር ምንድነው? የኢምፕላንት ፊልድ ከፍተኛ ብቃት እና የካበተ ልምድ የሚጠይቅ ፊልድ ነው፣ ስለሆነም፣ በ “ክላሊት ስማይል” ኢምፕላንቶችን መከወን ለስፔሻሊስት የጥርስ ሐኪም ብቻ የተፈቀደ መሆኑን የሚገልፅ የውስጥ አሰራር አለን። ቀጣይነት ያላቸው ሱፐርቪዥኖችም ምርጥ እና ፕሮፌሽናል ህክምናን ማቅረብ አስችሎናል፣ ከዚህ ጎን ለጎን ከፍተኛ ጥራት ያላቸው መሳሪያዎችን እና ቁሶችን እንጠቀማለን።
በጎልማሶች የጤና ጥቅል የጥርስ ህክምና በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ በእያንዳንዱ የ “ክላሊት ስማይል” የጥርስ ክሊኒኮች የሚሰጥ ሲሆን፣ ከዚህ በተጨማሪ በስምምነታችን መሰረት፣ በ “ክላሊት ስማይል” ሙሉ በሙሉ ሱፐርቪዥን የሚደረግባቸው የግል ክሊኒኮች፣ እና የጤና ሚኒስቴር አሰራርን በመከተል፣ ከፍተኛ የጥራት ደረጃ የማቅረብ ግዴታ ያለባቸው ናቸው።
ስለ እያንዳንዶቹ ወደ 70 የሚጠጉ “ክላሊት ስማይል” የጥርስ ክሊኒኮች መረጃ ለማግኘት በ “ክላሊት” ድረገፅ ላይ የጤና ባስኬት ሲስተም ይግቡ።
ለህክምና የሚያመለክቱት እንዴት ነው?
በ WhatsApp ፤ የፅሁፍ መልዕክት SMS ይላኩልን
በ ድረገፅ፤ በ “ክላሊት” ድረገፅ አፕሊኬሽን ከጥርስ ሐኪም ጋር ቀጠሮ ይያዙ
በስልክ፤ በአካባቢ ወይም ማግኘት በፈለጉት የህክምና አይነት የ “ክላሊት ስማይል” ክሊኒክን ይፈልጉ።
כללית סמייל